1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመኢአድና ሠማያዊ ፓርቲ ከሰሜን አሜሪካ መልስ መግለጫ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 23 2010

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምኅፃሩ (መኢአድ) እና የሠማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንቶች የልዑካን ቡድናቸውን በመምራት በሰሜን አሜሪካ የአራት ወራት የሥራ ጉብኝት አድርገው ተመልሰዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ስላደረጉትም ለዶይቸ ቬለ ገልጠዋል።

https://p.dw.com/p/2qBkk
Äthiopien | AEUP Vorsitzender Dr. Bezabeh Demisse
ምስል Getachew Tedla HG

መኢአድና ሠማያዊ ፓርቲ ስለ ሰሜን አሜሪካ ቆይቸው ተናገሩ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምኅፃሩ (መኢአድ) እና የሠማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንቶች የልዑካን ቡድናቸውን በመምራት በሰሜን አሜሪካ የአራት ወራት የሥራ ጉብኝት አድርገው ተመልሰዋል። ፓርቲዎቹ በሰሜን አሜሪካ ቆይታቸው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ ከማስረዳትም ባሻገር ከአሜሪካ መንግሥት ጋር ወደፊት ስለሚኖረው ግንኙነትም መምከራቸውን ለዶይቸ ቬለ ገልጠዋል። ትልቅ የፖለቲካ ኃይል ያለው አማራጭ የፖለቲካ ድርጅት ለመፍጠር በእንቅስቃሴ ላይ መኾናቸውንም ተናግረዋል። የኹለቱም ፖርቲዎች ፕሬዚዳንቶችን በማነጋገር ጌታቸው ተድላ ኃይለ-ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ የሚከተለውን አጠናቅሮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ