የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወቀሳ
ሐሙስ፣ መስከረም 11 2004ማስታወቂያ
ስደተኞቹ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዋና ከተማይቱ ሰንዓ አልፎ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊውን ከለላ እና ትብብር እንደማያደርግ ለጂዳው ወኪላችን ለነብዩ ሲራክ በስልክ ነግረውታል ። ትናንት ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በሰንአ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ አምደ ሚካኤል አድማሱ ግን ኤምባሲው ከ ዓለም ዓቀፍ የስደተኞች ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር IOM ጋር በመተባበር ስደተኞቹን እየረዳ መሆኑን ተናግረው ነበር ።
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ