የመን እና አሳዛኙ የጀልባ ስደተኞች ዕጣ28 ጥቅምት 2001ዓርብ፣ ጥቅምት 28 2001በትንሾቹ የአሳ ማስገሪያ ጀልባዎች የኤደንን ባሕረ ሰላጤ ተሻግረው ወደ የመን ለመግባት ሲሞከሩ ሰጥመው ህይወታቸውን ያጡ ስድሳ የጀልባ ስደተኞች አስከሬኖች በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በየመን ጠረፍ አቅራቢያ መገኘቱን ድንበር የማይገድበው የሀኪሞች ድርጅት MSF አስታወቀ።https://p.dw.com/p/FpNJሶማልያና የኤደን ባሕረ ሰላጤምስል APማስታወቂያበየመን የሚገኙት የድርጅቱ ባለስልጣን አንድሪያስ ኩፒፓስ ለዶይቸ ቬለ ያማር ኛ ክፍል እንዳስረዱት፡ ስደተኞቹ የሞቱት ህገ ወጦቹ የጀልባዎቹ ሰራተኞች በተለያየ ምክንያት ባሕር ውስጥ እንዲዘሉ ባስስገደዱበት ጊዜ ነበር። አርያም ተክሌ