የመንገድ አጠቃቀም ደህንነት
እሑድ፣ መጋቢት 28 2006ማስታወቂያ
ያለፈዉን ዓመት የዓለም የመንገድ ደህንነትን በሚመለከት ይፋ የሆነ ዘገባ በተሽከርካሪ የሚደርስ አደጋ ብዛት ተቀባይነት እንደሌለዉ ያመለክታል። የ182 ሃገራትን የመንገድ ደህንነት የቃኘዉ ይህ ዘገባ በየዓመቱ 1,2 ሚሊዮን ሕዝብ በዓለም ዙሪያ በአደጋ ህይወቱን እንደሚያጣ ገልጿል። ለአደጋ ከሚያጋልጡ ዋና ምክንያቶችም ጠጥቶ ማሽከርከርና ፍጥነት፤ ግንባር ቀደሞቹ ናቸዉ። ኢትዮጵያ ምንም እንኳን አዉቶሞቢል በመፈብረክ ባትታወቅም የመኪና አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ከሚገኝባቸዉ ሃገራትን አንዷ መሆኗ ይነገራል። በሀገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰፋፊና ምቹ መንገዶች ከመገንባታቸዉ ጋ በተያያዘም በፍጥነት ማሽከርከር እንዲሁም የመንገድ አጠቃቀም፤ የቴክኒክ እክል ያለባቸዉ ተሽከርካሪዎች ለሥራ መሠማራት አደጋ እንዲደጋገም ምክንያት ሆነዋል። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት ለዉይይት ያቀረበዉ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የመንገድ ደህንነትና ጥንቃቄን ይመለከታል።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ