የመንና የአጥፍቶ ጠፊው ጥቃት14 ግንቦት 2004ማክሰኞ፣ ግንቦት 14 2004በየመን መዲና ሰንዓ ትናንት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በጣለው የቦምብ ጥቃት ቢያንስ ዘጠና ሰዎች ተገድለው ከሁለት መቶ የሚበልጡ ቆስለዋል። ለጥቃቱ በየመን የሚንቀሳቀሰው የአልቓይዳ ቡድን ኃላፊነቱን ወስዶዋል።https://p.dw.com/p/150Asምስል Reutersማስታወቂያ የጥቃቱ ዒላማ ሰሜን እና ደቡብ የመን እንደገና ለተዋኃዱበትና በዛሬው ዕለት ለተከበረው ሀያ ሁለተኛ ዓመት ክብረ በዓል የሰልፍ ዝግጅት ያደርጉ የነበሩ አንድ የጦር ኃይሉ ቡድን አባላት ነበሩ። እና ጥቃቱ ከተጣለ በኋላ በሀገሪቱ በተለይም በመዲናይቱ ሰንዓ ትልቅ ውጥረት እንደሚታይ ቀደም ሲል ያነጋገርኩት የጄዳው ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ ገልጾልናል። ነቢዩ ሲራክ አርያም ተክሌ ተክሌ የኋላ