1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመሰብሰብ ነፃነት ድንጋጌ እና ቡድን 20

ዓርብ፣ ሰኔ 30 2009

«ጀርመናዉያን ሁሉ ያለ ምንም ምዝገባ እና ፈቃድ እንዲሁም የጦር መሣሪያ ሳይይዙ በሰላማዊነት የመሰብሰብ ነፃነት አላቸዉ።» በማለት ይጀምራል የጀርመን ሕገመንግስት አንቀጽ 8።

https://p.dw.com/p/2gArl
Deutschland Hamburg G20 - Elbphilharmonie
ምስል picture-alliance/dpa/D. Reinhardt

Der G20-Gipfel und das Grundgesetz - MP3-Stereo

እንዲያም ሆኖ ዓርብ ዕለት በሀምቡርግ ከተማ የሚጀምረዉ የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤን የሚመለከተዉ ወሳኝ አንቀጽ ደግሞ «ሜዳ ላይ ለሚካሄድ ስብሰባ ግን ይህ መብት በሕግ  ወይም በአንድ ሕግ መሠረታዊ ምክንያት ገደብ ሊደረግበት ይችላል።» ይላል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ የማይገደብ መሠረታዊ መብት አይደለም ማለት ነዉ። በዚህም ምክንያት ከተዘጋ ክፍል ዉጭ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች በፖሊስ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

በሃምቡርግ ከተማ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት 20 ሃገራት በያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ ሁለት ቀናት ከሚካሄደዉ ጎን ለጎን የተቃዉሞ ስብሰባ እና ሰልፎችን ለማድረግ የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ዉዝግብ አስነስቷል። ከምንም በላይ ጀርመኖች የሀገራቸዉ ሕገ መንግሥት የሚደነግግላቸዉ መብት እንዳይነካ አጥብቀዉ እየሞገቱ ነዉ። የመሰብሰብ ነፃነት ተግባራዊነት ስለመሰብሰብ እና ክልከላን ስለማንሳት በሚደነግገዉ አንቀጽ መሠረት የሚወሰን ነዉ። ይህም በ33ኛዉ አንቀጽ ላይ ይገኛል። በትክክል ተግባራዊ መደረጉን በተመለከተ የሚነሳዉ ክርክር የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለዉ ሲሆን በዚህ መሠረት በጀርመን ምክር ቤት ማለትም ቡንደስታኽ በጎርጎሪዮሳዊዉ 1953 እንዲሁም በ2008ዓ,ም ማሻሻያዎች ተደርገዋል። በዚህ ጉዳይም የሚካሄዱ ዉዝግቦችን በፍርድ ቤት በየዕለቱ ያስተናግዳሉ። የተቃዉሞ እንቅስቃሴ አዘጋጆች ስብሰባዉ የሚካሄድበትን ጊዜ እና የት አካባቢ እንደሚደረግ የመሳሰለዉን በማቅረብ ይከራከራሉ።

Deutschland Hamburg - G20 Proteste
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Schrader

እንዲያም ሆኖ ሃምቡርግ ላይ ዓርብ እና ቅዳሜ ዕለት የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ ሲካሄድ ፖሊስ 38 ስኩየር ኪሎ ሜትር የሚሆን አካባቢ ላይ እንዲህ ላሉት ስብሰባዎች እንዳይካሄዱባቸዉ አግዷል። የተከለከለዉ አካባቢዉ ከሰሜናዊ ሀምቡርግ የአዉሮፕላን ማረፊያዉ አንስቶ ጉባኤዉ የሚደረግበት ማዕከል ድረስ ይደርሳል። ፖሊስ በተሰብሳቢዎች፤ በፖሊስ ኃይሎችም ሆነ በሌላ በሦስተኛ አካል ላይ አደጋ ሊደርስ ይችላል በሚል የወሰደዉ ርምጃ መሆኑን ይናገራል። ተሞክሮዉንም ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ እንዲህ ያሉ ትላልቅ ጉባኤዎች መዉሰዱንም ያስረዳል። በርሊን የሚገኙት ሕገ ባለሙያ ክርስቲያን ፔስታሎሳ በሕግ የረደነገገዉ መሠረታዊዉ የመሰብሰብ ነፃነት የሕዝብን ፀጥታ የሚያሰጋ ነገር ሲኖር ሊታገድ የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ።

«በመሠረቱ ሕገ መንግሥታዊ የሆነ የመሰብሰብ ነፃነት አለ፤ ነገር ግን የሕዝብን ፀጥታ እና ሥርዓትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሊታገድ የሚችልበት አጋጣሚ አለ።»

እሳቸዉ እንደሚሉትም ሀምቡርግ ላይ ፖሊስ ለመሰብሰቢያ አይሆንም ብሎ ሰፊ አካባቢ ቢከልልም አሁንም የተቃዉሞዉን እንቅስቃሴ ለሚያደርጉት በቂ ስፍራ አለ። ይህ ግን ለመሠረታዊ መብቶችና ዴሞክራሲ የሚታገለዉ ኮሚቴ ባልደረባ ለኤልከ ስቴፈን ተቀባይነት የለዉም። የእሳቸዉ ኮሚቴ በዚሁ ምክንያት የሀምቡርግ ከተማ ፖሊስ ላይ ክስ መሥርቷል።

«ይህ የሚጀምረዉ፤ ከወራት በፊት አንስቶ በርከት ያሉ አመጽ የተቀላቀለ ርምጃ ለማካሄድ ካሰቡ ተንቀሳቀሶች ማስጠንቀቂያ ወደሃምቡርግ ከተማ መጥቷል። ይህን ምክንያት አድርገዉ ነዉ ይህን መብት ለመገደብ የወሰኑት። ስለዚህም መነሻዉ እዉነት አይደለም ማስረጃም ሊቀርብበት አይችልም።»

Deutschland Hamburg - G20 Proteste
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Schrader

የቡድን 20 ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት የሚካሄዱ ስብሰባዎችን አስመልክቶ በሕግ ጉዳይ ክርክር ነበር። የከተማዋ አስተዳደርም ሆነ የፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ግን ተመሳሳይ ነዉ። መጀመሪያ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ማካሄጃ ድንኳኖች  እንዳይቆሙ ታግዶ ነበር። ቆይቶ ግን ተፈቀደ። እንዲህ ያለዉ የዉሳኔ መቀያየር የሚያጋጥመዉ ሕጋዊዉን ጉዳይ ከመረዳት ጋር ይገናኛል ባይ ናቸዉ ክርስቲያን ፔስታሎሳ።  ኤልከ ሽቴፈን በበኩላቸዉ እርግጥነዉ የፀጥታ ጉዳይ ሁሉንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ ነዉ፤ ግንደግሞ በምናልባት ላይ ተመሥርቶ የሚወሰን ዉሳኔ ሁሉ መሠረታዊ መብትን እንዳይጋፋ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል በማለት ይሞግታሉ።

«ለፀጥታ አደገኛ የሆነ ማናቸዉንም ነገር ላይ ጥንቃቄ ማድረጉ በእርግጥ አስፈላጊ ነዉ። ነገር ግን ይህ ተጨባጭ በሆኑ ነጥቦች ላይ መሠረት በማድረግ እንጂ ሊሆን ይችላል በሚል ግምት ላይ መመሥረት የለበትም።  ግምትን በተመለከተ ብዙ ነገር ሊገመት ይችላል። አሁን ታዲያ ምንም አይነት አደጋ ሊያስከትሉ የማይችሉ ትናንሽ ስብሰባዎችም ይከለከላሉ ማለት ነዉ። በእርግጠኝነት የጉባኤ ሂደት  የማደናቀፍ ፍላጎት የለም።»

Deutschland Hamburg - G20 Proteste
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Schrader

በቡድን 20 ጉባኤ ወቅት የተቃዉሞ ድምጽ ከሚሰማባቸዉ ጉዳዮች አንዱ የአቶም የኃይል ማመንጫ ተቋም የመገንባት እቅድን ይመለከታል። በጎርጎሪዮሳዊዉ ከ1976ዓ,ም አንስቶም በሰሜን ምዕራብ ሃምቡርግ የአቶም ተቋም ግንባታን የሚቃወም ሰልፍ ሲካሄድ ኖሯል። በጀርመን ሕገ መንግሥት አንቀጽ 8 ላይ ስብሰባ ማካሄድ የሚፈልገዉ አካል የት እና እንዴት መሰብሰብ እንዳለበት መወሰን ይችላል የሚል ሕግ ሰፍሯል። ኤልከ ሽቴፈን ግን ይህን ሀምቡርግ ላይ የታየዉን አጋጣሚ በመንተራስ ተጋኗል ይላሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ