የመሬት ቅርምትና እና የምግብ ዋስትና ዕጦት
ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2003ማስታወቂያ
በዚህ የመሬት መቀራመትም ለነዳጅ ምርት ወይም ለከብቶች መኖ የሚሆኑ ሰብሎችን ለማምረት ሰፊ ቦታ ስለሚወስድ የአገሬው ተወላጅ ገበሬዎች እምብዛም ቦታ የላቸውም። ዳቦ ለዓለም የተሰኘው የጀርመን ወንጌላውያን የዕርዳታ ድርጅት እና FIAN በሚል ምህፃር የሚታወቀው መረጃ አቅራቢው የሰብዓዊ መብት ድርጅት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚል ፈሊጥ የተጀመረው የመሬት መቀራመት አደገኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አሳስበዋል። ነገ የሚታሰበውን የዓለም የምግብ ቀን ምክንያት በማድረግ ድርጅቶቹ የዓለማችንን ረሀብተኛ ቁጥር ለመቀነስ ትራፊ ለማጋባሰ ከሚወሰድ ዕርምጃ ይልቅ በሀገር ውስጥ አስፈላጊ ለሆነ ምርት ቅድሚያ እንዲሰጥ አስገንዝበዋል ።
Sabine Ripperger
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ