የመራጮችን መብት የሚጋፉ ድርጊቶች ተከሥተዋል መባሉ፣4 ግንቦት 2002ረቡዕ፣ ግንቦት 4 2002ቀደም ሲል ከዓለም ዜና እንዳዳመጣችሁት፣ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ምርጫ 12 ቀናት ቀርተውት ሳለ፣ ነፍስ እስኪጠፋ ድረስ የማዋከቡ እርምጃ የቀጠለ መስሏል። ስሞታውና እርስ-በርስ መካሰሱም እንዲሁ!https://p.dw.com/p/NLWBምስል APማስታወቂያየግንቦት 15 ምርጫ ከመድረሱ በፊት፣ እየዞሩ «ኢህአዴግን እንደምትመርጡ፣ በፊርማ አረጋግጡልን» በማለት፣ የሐረር ብሔራዊ ማኅበር ሰዎች፣ የተመዘገቡ መራጮችን የሚያስጨንቁ ድርጊቶች ይፈጽማሉ መባሉን ፣ ከድሬዳዋ፣ ስሞታ አቅራቢዎችንና ስሞታ የቀረባበባቸውን በማነጋገር ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል። ተክሌ የኋላ ሒሩት መለሰ