የሕፃናት ጤናና ህክምናዉ በኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ ጥር 14 2005ማስታወቂያ
ለሕፃናት የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማትና አገልግሎቱም የሕፃናትን ህይወት የሚቀጥፎ በሽታዎችን ለመከላከል በተለይ በገጠር አሳሳቢነቱ አሁንም እንዳለ ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚወለዱ ሕፃናትን በተለይ ደግሞ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚያጠቁ በሽታዎች ተቅማጥ፤ ኩፍኝና ወባ አልፈዉ ተርፈዉ የብዙዎችን ህይወት በመቅጠፍ ይጠቀሳሉ።
በተለይ ደግሞ የሕፃናት ሃኪምና የዚሁ ዘርፍ ህክምና መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ቦጋለ ወርቁ ዋነኛዉ የሳንባ ምች መሆኑን ይገልፃሉ።
በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት የሚወለዱባት ሀገር ኢትዮጵያ ያሏት የሕፃናት ሃኪሞች ቁጥርና የህክምና ይዞታዉ እንዴት ነዉ ባለሙያዉን አነጋግረናል። ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ