የሕወሓት 40ኛ የምሥረታ ዓመት አከባበር በመቀሌ
ረቡዕ፣ የካቲት 11 2007ማስታወቂያ
በዛሬው የመቀሌ በዓል ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የትግራይ ሕዝብ በመጪው ምርጫ እርሳቸው ትምክህተኛ እና ጠባብ ኃይሎች፣ እንዲሁም፣ የነርሱ ደላሎች ያሉዋቸውን የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንዲያሳፍራቸው ጥሪ አቅርበዋል። በበዓሉ የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር ፣ ያካባቢ ሀገራት መሪዎች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ