1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕንድ ሐኪሞች ርዳታ ለኢትዮጵያዉያን

ዓርብ፣ ኅዳር 6 2006

ሐኪሞቹና ረዳቶቻቸዉ አዲስ አበባና ደብደረ ብርሐን ከተሞች በሚገኙት ሆስፒታሎች ዉስጥ በማሕፀን፥ በኩላሊትና በአይን ሕመም ይሰቃዩ ለነበሩ በሺሕ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የቀዶ ሕክምና ርዳታ አድርገዋል

https://p.dw.com/p/1AIZF
ምስል picture-alliance/dpa

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰነበተ አንድ የሕንድ የሐኪሞች ቡድን በተለያዩ በሽታዎች ለሚሠቃዩ በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በነፃ አከመ።ሐኪሞቹና ረዳቶቻቸዉ አዲስ አበባና ደብደረ ብርሐን ከተሞች በሚገኙት ሆስፒታሎች ዉስጥ በማሕፀን፥ በኩላሊትና በአይን ሕመም ይሰቃዩ ለነበሩ በሺሕ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የቀዶ ሕክምና ርዳታ አድርገዋል።ለኢትዮጵያዉያን ሐኪሞችም ሥልጠና ሠጥተዋል። ደብረ ብርሐን ሆስፒታል ዉስጥ ብቻ ከአንድ ሺሕ የሚበልጡ የአይን ሕመምተኞች መታከማቸዉ ተዘግቧል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ