1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልጅ ሞት የጠራዉ ተልዕኮ

ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2003

ልጃቸዉን ያጡት በደም ካንሰር/ነቀርሳ/ ወይም ሊኩሚያ በሽታ ነዉ።

https://p.dw.com/p/PIPF
ካንሰር/ነቀርሳን/ለመታደግ ምርምር በየደረጃዉ ይካሄዳል

እራሳቸዉ እንደሚገልፁት ሁለት ልጆችን ወልደዉ ለአስር ዓመታት ቆይተዋል፤ ለአራት ዓመታት ብቻ አብሯቸዉ የቆየዉን ተወዳጅ ልጅ ለመዉለድ። ያ ልጅ ግን እንደአንዳንድ ብርቅዬ መሰሎቹ የቤተሰቦቹ ሆኖ የቆየዉ ለጥቂት ዓመታት ብቻ ነዉ። እሱን ማጣታቸዉ በካንሰር ላይ የማይቆም ጦርነትን እንዲያዉጁ አነሳሳቸዉና በስሙ አንድ ማኅበር አቋቋሙ፤ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ማኅበረሰብ በሚል። ማኅበራቸዉ በተለይ በዚህ በሽታ ለሚጠቁ ልጆች አብነት ለማፈላለግ ይጥራል፤ ኅብረተሰቡ ባጠቃላይ ደግሞ ስለበሽታዉ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረዉ በሚችለዉ መንገድ ሁሉ መረጃዎችን ያሰራጫል። ለጋ ተቋም እንደመሆኑ አቅሙ በሁሉ ረገድ ማጠናከር ይጠይቃል፤ በኢትዮጵያ የካንሰር ማለትም የነቀርሳ ተጠቂዎችን ለመታደግ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ