1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልጅነት ልምሻን የማጥፋት ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2005

የዓለም የልጅነት ልምሻ ዕለት ባለፈዉ ሳምንት ታስቧል። ዘንድሮ ዕለቱ ሲታሰብ ይፋ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ይህበሽታም እንደፈንጣጣ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከምድርገፅ ጠፍቷል እንዳይባል ሶስት ሀገሮች ላይስጋቱ አልቀነሰም።

https://p.dw.com/p/16ZiN
ምስል AP Photo

ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሽታዉ አልታየም የዘመቻ ክትባቱም የፖቀጥሏል። የልጅነት ልምሻ ማለትም ፖሊዮን የማጥፋት መርሃግብር ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ሲቋቋም በወቅቱ ይህ በሽታ በዓመት ከ350 ሺህ በላይ ሰዎችን አካል ያሽመደምድ ነበር። መርሃግብሩ ተነድፎ ዘመቻዉ ተጠናክሮ ይህን የአካል ጉዳት የሚያስከትለዉን በሽታ ለመከላከል የሚያስችለዉ ክትባት በመሰጠቱ ዛሬ ከአፍሪቃ እና እስያ በቀር በቀሪዉ ክፍል ዓለም ታሪክ መሆኑ ነዉ የሚነገረዉ።

Impfungen gegen Kinderlähmung in Pakistan
ምስል picture-alliance/dpa

በተጠቀሱት ክፍለ ዓለሞችም ቢሆን ከችግሩ ያልተላቀቁት ብዙ የሚባሉ አይደሉም፤ አፍሪቃ ዉስጥ ናይጀሪያ፤ እስያ ደግሞ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን። በጤና ዘርፍ ምርምር የሚያካሂዱ ባለሙያዎች አጋጣሚዉ ይህንንም በሽታ እንደፈንጣጣ ሁሉ ታሪክ የሚሆንበት ጊዜ መቃረቡን ያመላክታል እያሉ ነዉ። በያዝነዉ የአዉሮጳዉያን ዓመት ናይጀሪያ ዉስጥ በስድስት ወራት 171 ሰዎች ላይ ብቻ ነዉ በሽታዉ የታየዉ። ከተጠቀሰዉ ቁጥር አብዛኛዉ ታማሚ ደግሞ የተገኘዉ ሙስና፤ አለመረጋጋት በተስፋፋበትና የበሽታዉ መከላከያ ክትባት በአግባቡ ባልተዳረሰባቸዉ የሰሜን ናይጀሪያ ግዛቶች ነዉ። ሁኔታዉ የአካባቢዉን ባለስልጣናት አሳስቧል።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ