1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላምፔዱዛ ተገን ጠያቄዎች አሳዛኝ ክስተት

ዓርብ፣ መስከረም 24 2006

በኢጣልያ ደሴት፤ ላምፔዱዛ አቅራቢያ ፣ ትናንት በእሳት ከተያያዛች በኋላ በሰጠመችው ጀልባ ውስጥ ከነበሩት ስደተኞች ደብዛቸው የጠፋውን ፍለጋ ዛሬም ቀጥሏል ።ከሊቢያ የባህር ጠረፍ 500 የሚሆኑ ስደተኞች አጭቃ ላምፔዱዛ የባህር ዳርቻ የደረሰችው ይህችው ጀልባ የኤርትራ እና የሶማሊያ ስደተኞች ነበር ያሳፈረችው ።

https://p.dw.com/p/19tpn
epa03894672 Bodies retrieved from the sea are pictured inside a hangar in Lampedusa, Italy, 03 October 2013. A boat carrying about 500 people from North Africa caught fire before reaching the Italian island of Lampedusa on 03 October. Rescuers recovered 82 bodies and reported at least 250 people were still missing. EPA/FRANCO LANNINO +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

የእነዚህ ሁለት የምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት ህዝቦች ለምን ከሀገራቸው ይሰደዳሉ? በአነስተኛዋ የኢጣልያ የባህር ጠረፍ ላንፔዱዛ ትናንት የደረሰዉ አሳዛኝ አደጋ፤ ከፍተኛ ድንጋጤን ዉስጥ ጥሏል፤ መፍትሄ አሳጥቶአል። በአደጋ ሰራተኞች ከባህር ላይ የተለቀመዉ አስክሪን በባህር ዳርቻዉ ላይ ተደርድሮ ይታያል። ከሟቾች መካከል በርካታ ሴቶች ህፃናት እንዲሁም ነፍሰ ጡር ሴቶች ይገኙበታል። ይህ ደግሞ አደጋዉን እጅግ መራራራና አስደንጋጭ ያደርገዋል። የተመ የስደተኞች መርጃ ድርጅት UNHCRእንዳስታወቀዉ በጎአ 2012 ብቻ 500 የጀልባ ስደተኞች ወደ አዉሮፓ ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ሜዲተራንያን ባህር ላይ ህይወታቸዉ አልፎአል። በኢጣልያዋ ቱርኒ ከተማ የሚገኘዉ በስደተኞች ጉዳይ ጥናት የሚያደርገዉ የዓለማቀፍ እና የአዉሮጳ ፍርድ ቤት ተጠሪ ፊሮቾ ባስቶሪ እንደሚሉት በየዓመቱ ሽዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ወደዚህ መምጣት መፈለጋቸዉ የሚያስደንቅ አይደለም፤

epa03894368 Italian rescue workers recover dead bodies from a boat at the port of Lampedusa, Italy, 03 October 2013. A boat packed with African migrants caught fire and sank off the southern Italian island of Lampedusa on 03 October. The bodies of 40 migrants have been found off Lampedusa, the Ansa news agency reported citing the coast guard, taking the death toll to at least 133. EPA/ETTORE FERRARI +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

« በሚያሳዝን ሁኔታ ጉዳዩ የቆየ ታሪክ ነዉ። ስደተኞቹ ከሚመነጩባቸዉ ወይም አቋርጠዉ ከሚመጡባቸዉ ሀገራት ጋር የተሳካ ትብብር ካለ የስደተኞቹ ቁጥር ሲቀንስ ይታያል፤ ትብብር ከሌለ ደግሞ ቁጥሩ በአንፃራዊ ሁኔታ ያድጋል። ምክንያቱ በነዚህ ሀገራት የፖለቲካ አመረጋጋት እና ዉጥረት በመኖሩ ነዉ»

በርካታ የሰሜን አፍሪቃ ሀገራት ዜጎች በጀልባ ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ይሞክራሉ ። እንደ ተመድ የስደተኞች ጉዳይ መስሪያቤት ገለፃ በያዝነዉ የጎ 2013 ዓ,ም የመጀመርያዎቹ ስድስት ወራቶች ብቻ 8400 ስደተኞች በጣልያን እና ማልታ የባህር ጠረፎች ደርሰዋል። ይህ ቁጥር ወደ አዉሮጳ ለመግባት የሞከሩና ባህር የበላቸዉን ሰዎች አያካትትም። ትናንት ላምፔዱዛ የባህር ጠረፍ አካባቢ የሰመጠዉ ጀልባ ላይ ተሳፍረዉ የነበሩት ስደተኞች ከሶማልያ እና ከኤርትራ የመጡ መሆናቸዉ ተነግሮአል። ዋና ቢሮዉን ሮም ጣልያን ያደረገዉ፤ አበሻ የተሰኘዉ መንግስታዊ ያልሆነ የርዳታ ድርጅት ተጠሪ አባ ሙሲ ዘርአይ ለምን ከእነዚህ ሀገራት ስደተኞች እንደሚፈልሱ ይገልፃሉ፤ « ከጎአ 1994 ዓ,ም ጀምሮ ሶማልያ ከቁጥጥር ዉጭ ሆና በተደጋጋሚ ጦርነት ዉስጥ ትገኛለች። በኤርትራ ያለዉን አምባገነንን ስርዓት ብዙዎች የአፍሪቃው ሰሜን ኮርያዉ ሲሉ ነው የሚጠሩት። ስለዚህ በኤርትራ በምንም መልኩ ነፃነት የለም። እነዚህ ሰዎች ሃገራቸውን ጥለው የሚወጡት አዲስ ህይወት፤ ነጻነት ና ዲሞክራሲ እንዲሁም ወደፊቱ ሌሎች እድሎችን ለማግኝት ነው»

epa03895672 Hearses disembark from a ferry in the harbour of Lampedusa, Italy, 04 October 2013. Italy mourned the 300 African asylum-seekers feared dead in the worst ever Mediterranean refugee disaster, as debate raged over Europe's flawed migration policy. Emergency services on the island of Lampedusa said they had recovered 111 bodies and plucked 155 survivors from the water from a boat with an estimated 450 to 500 people on board. EPA/FRANCO LANNINO
ምስል picture alliance/dpa

የተገን ጠያቂዎች ችግር የሚጀምረዉ ከትዉልድ ሀገራቸዉ በመሆኑ፤ የአፍሪቃዉ ሕብረት በአፍሪቃዉ ቀንድ ያለዉን ቀዉስ እና ጦርነት ለመፍታት መሥራቱ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አባ ሙሴ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት ነዉ ትዉለደ ኤርትራዊዉ አባ ሙሴ አንድ የእርዳታ ድርጅት በጣልያን ሮም ላይ ያቋቋሙት። ድርጅቱ በአዉሮጳ የሚኖሩ ተገን ጠያቂዎችንም በመርዳት ይታወቃል። ትናንት የአዉሮጳ ኮሚሽን የዉስጥ ጉዳዮች ተጠሪ ሲሲሊያ ማልምስቶርም ወደ አዉሮጳ፣ በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን በሚያሸጋግሩ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ አለበት ብለዋል። በአባ ሙሴ አስተያየት ግን ይሄ የተሳሳተ አባባል ነው ። « የአዉሮጳ ሃገራት በህገ ወጥ መንገድ ስደተኞችን የሚያሸጋግሩ ሰዎችን ለማስቆም ለመከላከል ከፈለጉ ብቸኛው መንገድ ተገን ጠያቂዎች በህጋዊ መንገድ እንዲገቡ በራቸዉን ክፍት ማድረግ ነው ። ባለፉት 10 ዓመታት የአዉሮጳ ፖሊሲ የሚያተኩረው ድንበራቸውን እንዴት መዝጋት እንዳለባቸው ነው ። ግን በሩ ሲዘጋ ሰዎችን ከሀገር ወደ ሌላ ፣ በህገ ወጥ መንገድ የሚያሸጋግሩ ሰዎች ፤ ለተገን ጠያቂዎቹ ሌላ መስኮት ይከፍታሉ ።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ