የሊቢያ አገናኝ ቡድን ጉባኤ
ዓርብ፣ ሐምሌ 8 2003ማስታወቂያ
በጉባኤው ላይ የተሳተፉት ኃያላኑ መንግሥታት ደግሞ የሊቢያውን መሪ የኮሎኔል ሞአመር ጋዳፊን ኃይሎች ለሚወጉት አማፅያን እውቅና ሰጥተዋል ። ከሰላሳ አገራት የተውጣጡ የኃያላኑ መንግሥታት ና ተሰሚነት ያላቸው የአካባቢው አገራት ተወካዮች የተሳተፉበት ይኽው ጉባኤ ጋዳፊን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረገውን ወታደራዊውን ጫና ለማጠናከርም ተስማምቷል ። ጉባኤው ሊቢያ ወደ ዲሞክራሲ እንድትሸጋገር ያስችላታል ያለውን የሰላም እቅድም አውጥቷል ። በሰላም እቅዱ ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪቃ ህብረት የሚቆጣጠሩት የተኩስ አቁም ተካቷል ። የጎሳ መሪዎችን እና በአሁኑ ሰዓት በጋዳፊ ቁጥጥር ስር ካለችው የትሪፖሊ ከተማ የተውጣጡ ተወካዮችን የሚያሳትፍ ብሔራዊ ጉባኤ የማካሄድ ሃሳብም ቀርቧል ። ከጉባኤው በመቀጠል በሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማስፈን ህገ መንግሥት ማርቀቅና የምክር ቤት ምርጫዎችን ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል ። የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ስለ ጉባኤው ሂደት ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ