የሊቢያ ህገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚቴና ተግባሩ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2006ማስታወቂያ
የሊቢያ አዲስ ህገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚቴ ምሥራቅ ሊቢያ ውስጥ ትናንት ሥራውን ጀመረ ። ከቤንጋዚ በስተምሥራቅ በምትገኘው ባይዳ በተባለችው ከተማ የተሰበሰቡት 47 ቱ አባላት ከሊቢያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተወከሉ መሆናቸው ተዘግቧል ።ህገ መንግሥቱን የማርቀቁ ሂደት ከተጠበቀው በላይ ጊዜ እንደሚወሰድ ይገመታል ። ህገ መንግሥቱን የሚያረቁት ተወካዮች በሃገሪቱ ስር እየሰደደ የሄደውን ፖለቲካዊና ጎሳዊ ግጭቶች በተለይ በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሚቀርበውን የተጠናከረ የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚኖርባቸው ተመልክቷል ። ረቂቁ እንደተጠናቀቀ ለህዝበ ውሳኔ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ። የዶቼቬለው አንድሪያስ ጎርትሴቭስኪ ያዘጋጀውን ዘገባ ይልማ ኃይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ