1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሆድ ህመም እና መንስኤዎቹ

ማክሰኞ፣ ጥር 10 2008

ሆዴን ቆረጠኝ፤ ሆዴን ነፋኝ፤ ብዙዎች በተደጋጋሚ የሚገልጿቸዉ የሆድ ህመም ምልክቶች ናቸዉ። ለሆድ ህመም ደግሞ የተለያዩ መንስኤዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የዉስጥ ደዌ ሃኪሞች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/1Hg8C
Symbolbild Magenschmerzen Bauchschmerzen
ምስል Colourbox/J. Sapic

የሆድ ህመም እና መንስኤዎቹ

ከአድማጮች ለሚቀርቡ ጤናነክ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት የሁልጊዜም ተባባሪያችን የሆኑት የዉስጥ ደዌ እና ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዙ በሽታዎች ላይ ለረዥም ጊዜ የሠሩት ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ፤ ለሆድ ህመም የሚዳርጉ ባክቴሪያዎች ዓይነታቸዉ ይለያያል ይላሉ። የህመሙ ምክንያቶች አሜባም ሆነ ጃርድያ ያሉ ጥገኛ ተሐዋሲያን ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ሁሉ ህመምተኛዉ ሀኪም ጋር ቀርቦ በሚደረግለት ምርመራ ነዉ ምንነቱ ሊጣራ የሚችለዉ። ጥያቄያቸዉን የላኩልን አድማጭ ከማብራሪያዉ እንደሚጠቀሙ ተስፋ እናደርጋለን፤ ሌሎቻችሁም ጤናነክ ጥያቄዎቻችሁን መላክ ትችላላችሁ፤ የሚመለከታቸዉን ሃኪሞች በእናንተ ስም እንጠይቃለን። ማብራሪያዉን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ