1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሆሎኮስት 70ኛ ዓመት መታሰቢያ

ማክሰኞ፣ ጥር 19 2007

የጀርመን ናዚዎች በሚሊዮን በሚቆጠሩ የአዉሮጳ ዜጎችን በየስፍራዉ ፈጅተዋል። በእሳት ማቃጠል ጨምሮ በተለያየ መንገድ ከተገደሉት ዉስጥ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/1ERFs
Merkel bei der zentralen Auftaktveranstaltung 70 Jahre Auschwitz Befreiung 26.01.2015 Berlin
ምስል picture-alliance/dpa/B. von Jutrczenka

የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ሕብረት ቀዩ ጦር የዛሬ ሰባ ዓመት በዛሬዉ ዕለት የአዉሽቪትዝ-ፖላንድን ማጎሪያ ጣቢያ ከናዚ እጅ ከማስለቀቁ በፊት በዚያ በትልቁ እስር ቤት ከአንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ሰዎች በላይ በጋዝ ታፍነዉ ተገድለዋል። የጀርመኑ ርዕሰ ብሔር ዮአኺም ጋዉክ ዕለቱን ለማሰብ ለተሰበሰበዉ የጀርመን ምክር ቤት (ቡንደስታኽ) ባደረጉት ንግግር ዘረኛነት፤ ጥላቻና እሱን ተከትሎ የመጣዉ የዘር ማጥፋት የፋሽስቶች ዘመቻ መረሳት የለበትም በማለት ትዉልዱ እንዲያስብበት አስጠንቅቀዋል። የበርሊኑ ዘጋቢችን ይልማ ኃይለሚካኤል ዝርዝር ዘገባ ይኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ