1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህንድ ዉቅያኖሱ ሱናሚ፣ አምስተኛ አመት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 15 2002

ልክ የዛሪ አምስት አመት ህንድ ዉቅያኖስን አናዉጦ በአካባቢዉ ያሉ አገራትን የመታዉ ሱናሚ ቢያንስ 230,000 ያህል ህዝቦችን ህይወት ቀጥፎአል። የባህር እና የዉቅያኖስ ነዉጥ በሰዉ ልጅ እና ንብረት ላይ ይህን ያህል የከፋ አደጋ ሲደርስ ከስከዛሪዉ ሁሉ የዛሪ አምስት አመት ህንድ ዉቅያኖስን የመታዉ ሱናሚ እጅግ ከፍተኛዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/LD01
ጃቫ ደሴት ኢንዶኔዥያምስል AP

የህንድ ዉቅያኖሱ የመሪት ነዉጥ አዋስኞቹን ስምንት የእስያ አገሮች ብቻ ሳይሆን ያጥለቀለቀዉ ምስራቅ እና የደቡብ ምስራቅ አፍሪቃ አገራትም ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሶአል። ከዚህ ከፍተኛ የዉቅያኖስ መጥለቅለቅ በኻላ ጀርመናዉያን ከኢንዶኒዥያ ጋር በመተባበር የባህር ነዉጥን በቅድሚያ ለማወቅ የሚረዳ መሳርያ ካቀረቡ በኻላ በአሁኑ ወቅት በርካታ ዉቅያኖስን የሚዋሰኑ አገራት ይህንን መሳርያ መገልገል ጀምረዋል።
ምዕራባዉያኑ የገና በአልን ለማክበር የስራ ግዜአቸዉን አጠናቀዉ የገና በአል እረፍታቸዉን በታይላንድ ለማሳለፍ ከብዙ አዉሮጻ አገራት ወደ ታይላንድ ኢንዶኔዥያ የባህር ዳርቻን ጸሃይ በመሞቅ እና ለመዋኘት ወርደዋል፣ በዉቅያኖሱ ዳርቻ ያሉ ሆቴሎች ጢም ብለዉ ሞልተዋል። የጠዋትን ጸሃይ ለመጋራት የዉቅያኖሱን ዉሃ ፉጨት ለማዳመጥ እንዲሁም ለመዋኘት ከአለም የተሰባሰበዉ ቱሪስቶች የአገሪዉም ህዝብ ቦታ ቦታዉን ይዞ ይዝናናል። እ.አ 2004 ታህሳስ 17 ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ላይ ነዉ በድንገት አነስ ያለ የመሪት መንቀጥቀጥ አይነት ሁኔታ ተሰማ ቀጠል ብሎ የህንድ ዉቅያኖስ በመናወጥ ገንፍሎ ሱናሚዉ ዉቅያኖሱ ዳርቻ ተቀምጠዉ የሚዝናኑትን ብቻ ሳይሆን 1000 ኪሎ ሜትር በላይ ያህል ዘልቆ የሰዉ ህይወት ቤት ንብረት ከተማን ያአጠፋዉ ያወደመዉ!
220,000 ያህል ህዝቦች በዚህ የዉቅያኖስ ነዉጥ አልቀዋል። 175,000 ያህል ሪሳ ቢቆጠርም 50,000ያህል ህዝቦች የደረሱበት አይታወቅም። በዝያዉ መጠን ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ህዝቦች መጠለያ አልባ ሆነዋል። በኢንዶኔዥያ ብቻ በተለይ በአቼ መንደር በሱማትራ ደሴት 127,000 ያህል ህዝቦች የዚሁ ሱናሚ ሰለባ ሆነዋል። በታይላንድም 5,400 ሰዎች ሰለባ ሲሆኑ አብዛኞቹ ከአዉሮጻ የመጡ ቱሪስቶች ናቸዉ። በስሪላንካ በህንድም 10,000 ሺ ያህል ሰዉ የዚሁ የዉቅያኖስ ነዉጥ ተጠቂ ነዉ። ህንድ ዉቅያኖስን በሚያዋስነዉ የአፍሪቃ ክፍልም እንዲሁ በርካቶች ህይወታቸዉን አተዋል።
የዛሪ አምስት አመት ህንድ ዉቅያኖስ ተናዉጦ ይህ ከፍተኛ አደጋ ካደረሰ ከጥቂት ወራቶች በኻላ በአካባቢዉ በጀርመን ኢንዶኔዥያ የጥምር ትብብር ከዉቅያኖስ በታች ያለዉን ነዉጥ አስቀድሞ የሚጠቁም መሳርያ በስራ ላይ ዋለ። በኢንዶኔዥያ ጃካርታ ከተማ የአየር ጸባይ መቆጣጠርያ ተቋም ተመራማሪ የሆኑት Horst Letz የህንድ ዉቅያኖስን በታች ያለዉን የመሪት ነዉጥን በግዜዉ ለማወቅ እና የሱናሚን አደጋ ለማምለጥ በየቦታዉ አስቀድሞ የሚጠቁም መሳርያ መተከሉን ያስረዳሉ። ይህ አስቀድሞ ከዉቅያኖስ በታች ያለዉ የመሪት መናወጡን የሚያሳይ መሳርያ በየአራት እና አምስት ደቂቃዉ የድምጽ ምልክት የሚያሳይ ሲሆን የሱናሚ ስጋት ሲኖር በአፋጣኝ በብዙሃን መገናኛ ለአካባቢ ቀበሌ ቢሮች በማስታወቅ ህዝቡ ራሱን ከአደጋ እንዲጠብቅ ይደረጋል። የደሴቶች ባለጸጋዋ ኢንዶኔዝያ በአንድ ቀን ብቻ አርባ ያህል ግዜ ለአደጋ የማያጋልጥ የመሪት መንቀጥቀጥ እንዳለ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ። ከዉቅያኖስ በታች የመሪትን መናወጥ አስቀድሞ የሚጠቁመዉን መሳርያ በአለም ዙርያ ዉቅያኖስ አዋሳኝ አገራት ላይ ለመትከል እና የጀርመን ኢንዶኔዥያዉን ተቋም ለማገዝ ቻይና፣ ጃፓን፣ ፈረንሳይ፣ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ድጎማ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በአለም ህዝብ ብዛት አራተኛ የሆነች እና 17 ሺ ግድም ደሴቶችን ያካተተችዉ ኢንዶኔዥያ በዉቅያኖስ ነዉጥ ተጠቂ በመሆንዋ የጀርመን ኢንዶኔዝያ የመሪት ነዉጥ አስቀድሞ ጠቋሚ ተቋም፣ ሱናሚ እንደሚከሰት የሚጠቁመዉን መሳርያ እስከ መጭዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት በየአገሪቷ ዙርያ ለማቆም ህዝቡዋን ከከፍ አደጋ ለመጠበቅ እቅድ ላይ ናት።
በኢንዶኔዥያ በተለይ በአቼ መንደር ሱማትራ ደሴት ላይ የዛሪ አምስት አመት ዉቅያኖስ ተናዉጦ ገንፍሎ ከፍተኛ አደጋ ያደረሰዉ ሱናሚ ቁስሉ አገግሞ ከተማዉ እንደገና ተገንብቶ ቦታዉ የቱሪስቶች መዝናኛ ሆንዋል፣ ምንም እንኻ ከዚህ አሰቃቂ የተፈጥሮ አደጋ ያመለጡ አሁንም አሰቃቂዉ ትዉስታ ከአዕምሮአቸዉ ጨርሾ ባይጠፋም፣ ዛሪ አምስት አመቱ የሱናሚ አዳጋ የጠፋዉን ህይወት በማስታወስ የኢንዶኔዥያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙርያ በቀኑ የሃዘን መታሰብያ ይደረጋል።

Bilder aus Aceh Indonesien 5 Jahre nach Tsunami Flash-Galerie
በአቼ ደሴት በመገንባ ላይ ያለዉ መስጊድምስል DW/Robina

አዜብ ታደሰ፣

ተክሌ የኋላ