1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሄይጉ ችሎት ዉሳኔና ያስከተለዉ ምላሽ

ሐሙስ፣ የካቲት 26 2001

በኔዘርላንድ ዘ ሃይግ የሚገኘዉ ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎት በሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር ላይ ትናንት ያሳለፈዉ የእስር ማዘዣ ከያቅጣጫዉ ምላሽ አስከትሏል። ቻይና ክሱ እንዲታገድ ስትጠይቅ፤ ኢራን ሚዛናዊ ያልሆነ ብላዋለች።

https://p.dw.com/p/H6GB
ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎት
ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎትምስል AP

አስቸኳይ ጉባኤ በዝግ የጀመረዉ የአፍሪቃ ኅብረት ዉሳኔዉ በሱዳን የተጀመረዉን የሰላም ሂደት ያደናቅፋል ሲል ተችቷል። ደቡብ አፍሪቃ በበኩሏ አሳዛኝ ብላዋለች። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸዉ ፕሬዝደንት አልበሽር ዉሳኔዉን በመቃወም ካርቱም ላይ ለሰልፍ ለወጣዉ ህዝባቸዉ ድርጊቱ የቅኝ አገዛዝ እቅድ ነዉ ሲሉ በማዉገዝ፤ አስር የሚሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ከአገራቸዉ እንዲወጡ ማዘዛቸዉን ተናግረዋል።