የሃይማኖት ግጭቶች የምክክር መድረክ
ሰኞ፣ ሰኔ 27 2003ማስታወቂያ
የዓለም የዕርቅና የሰላም ግብረ ሠናይ ድርጅት የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሊቀ መንበር ዶክተር ያዕቆብ በቀለ በቅርቡ ስለ ደረሱ የሃይማኖት ግጭቶች መንስኤ ከዶቼቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ቃለ ምልልስ የችግሩ መነሻ ህብረተሰቡ ስለ ሃይማኖቱ የጠለቀ እውቀት አለመጨበጡ መሆኑን ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ በተለያዩ ጉዳዮች ሰበብ የሚነሱ ግጭቶችን በእርቅና በሽምግልና ለመፍታት የሚንቀሳቀሰው የዓለም የሠላምና የእርቅ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባላፈው አርብ አዲስ አበባ ውስጥ በኢትዮጵያ በየጊዜው የሚነሱ የሃይማኖት ግጭቶችን በተመለከተ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ