የሃኖፈሩ የኢንዱስትሪ ትርዒት፣ ሥነ-ቴክኒክና ታዳሽ የኃይል ምንጭ፣
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2001ማስታወቂያ
የሥነ-ቴክኒክ ትርዒት ፣ ባለፈው ሰኞ የተከፈተ ሲሆን እስከፊታችን ዓርብ ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል። ትርዒቱን ባለፈው ሰኞ፣ መራኂተ-መንግሥት ወ/ሮ አንጌል ሜርክል 2 ሰዓት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
«በቀውስ ውስጥ እየኖርን እንዲሁ አንመለከትም። የኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ተጠናክረው ችግሩን እንዲወጡት እንፈልጋለን። በዚህ በሃኖፈሩ ትርዒት የዚህን የማገገም ምልክት ዐይቼአለሁ። መለስተኛ የኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ትንንሸቹም ሆኑ ትልልቆቹ፣ ከባዱን የኤኮኖሚ ችግር ተቋቁመውና የደቀነውን ቅድመ-ግዴታ አሟልተው አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ይዘው ቀርበዋል። »
በዘንድሮው የሃኖፈር የኢንዱስትሪ ትርዒት ልዩ እንግዳ በመሆን ትርዒቷን በማቅረብ ላይ የምትገኘው ሀገር በሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ፣ በኤኮኖሚም እመርታ ያሳየችው ደቡብ ኮሪያ ናት።
ተክሌ የኋላ፣
አርያም ተክሌ፣