1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሃማስ ፋታህ ስምምነትና የእስራኤል ቅሬታ

ረቡዕ፣ ጥር 30 2004

የፍልስጤም ተቀናቃኝ ኃይሎች ፋታህና ሃማስ በመጪዉ ግንቦት ወር ምርጫ ለማካሄድ በመወሰን፤ አብሮ ለመሥራት ስምምነት መፈራረማቸዉ እስራኤልን አስቆጥቷል። ኳታር ዶሃ ላይ ከትናንት በስተያ ስምምነቱ ሲደረስ፤ እስራኤል በበኩሏ ከፍልስጤም ጋ የተጀመረዉ

https://p.dw.com/p/13zsD
ማሕሙድ አባስና ኻሊድ ማሻል በኳታርምስል picture-alliance/dpa

የሰላም ድርድር አበቃለት ብላለች። እስራኤልን በሚመለከት የተራራቀ አቋም የሚያራምዱት ተፃራሪዎቹ ሃማስና ፋታህ በስምምነታቸዉ እስከምን እንደሚዘልቁ ለጊዜዉ ባይገለጽም፤ የፍልስጤም ህዝብ ግን ርምጃዉን ደግፎታል። በአካባቢዉ ሰላም ላይ ሊኖረዉ የሚችለዉን ተፅዖኖና ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት ሃይፋ የሚገኘዉ ወኪላችንን ግርማዉ አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ግርማዉ አሻግሬ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ