የሂዩማን ራይትስ ዎች ዓመታዊ ዘገባ
ማክሰኞ፣ ጥር 13 2006ማስታወቂያ
መቀመጫውን ኒዮርክ-ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ሂዩማን ራይትስ ዎች እንደሚለው በዚህ ዓመት ይበልጥ ጎልቶ የታየው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጦርነት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተከሰቱ የመብት ጥሰቶች ናቸው። እነዚህም የሰላማዊ ሰዎች ግድያን ጨምሮ ዘረፋና ስደት የመሳሰሉ ጥቃቶችን እንደሚያጠቃልል ሪፖርቱ ኣመልክቷል።
በሂዩማን ራይትስ ዎች የኣፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንዔል በቀለ እንደሚዘረዝሩት የኢትዮጵያ መንግስትም የጸረ ሽብር እና የሲቪክ ማህበራት ህግጋትን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተከሷል።
በተለይም የኤርትራ መንግስት ደግሞ ለዓለም ህብረተሰብ በሩን ከመዝጋት ኣንስቶ ያለፍርድ ቤት መታሰር እና ሌሎች በርካታ ሰቆቃዎችን በመፈጸም እጅግ የተበላሸ ሪኮርድ ተሰቶታል ተብሏል።
ጃፈር ዓሊ
ሂሩት መለሰ