1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሂውመን ራይትስ ዎች ዓመታዊ መግለጫ

ዓርብ፣ ጥር 8 2001

መንበሩ ኒው ዮርክ የሚገኘው ሂውመን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ በተለያዩ ሀገሮች የመብዓዊ መብት ጥሰት መድረሱን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/GZFT
የሂውመን ራይትስ ዎች
የሂውመን ራይትስ ዎች

ዘገባው እንዳስረዳው፡ የተሰናባቹ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ዳብልዩ ቡሽ መስተዳድር ሰብዓዊ መብት ከማስከበር ይልቅ በተለያዩ ሀገሮች ሰብዓዊ መብት ሲጣስ በዝምታ አልፎዋል። በመሆኑም፡ በቅርቡ ስልጣን የሚረከበው የባራክ ኦባማ መስተዳድር ለሰብዓዊ መብት ከበሬታ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ የሂውመን ራይትስ ዎች ከፍተኛ ባለስልጣን ኬንስ ሮት አደራ ብለዋል።