1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀገር ፍቅር ቀን በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 3 2009

አስተያየት ከጠየቅናቸዉ አንዳንዶች ስለተባለዉ አከባበር ያልሰሙ፤ ሌሎቹም የፖለቲካ ዉጥረት የፈጠረዉ ሳይሆን እንዳልቀረ የገመቱ፤ ስለሀገር ፍቅር መታሰቡ ቢዘገይም አዎንታዊ እንደሆነ ገልጸዉልናል።

https://p.dw.com/p/2jbvx
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የኢትዮጵያ መንግሥት መጪዉን 2010ን ለመቀበል ባቀደዉ የ10 ቀናት የአዲስ ዓመት አከባበር የዛሬዉን ዕለት የሀገር ፍቅር ቀን ብሎ ማክበሩ ተሰምቷል። የመንግሥት መገናኛ ዘዴ እንደዘገበዉ ዕለቱን ዜጎች ለሀገራቸዉ ያላቸዉን ፍቅር የሚገልፁበት ባለዉ ዕቅድ መሠረት የበዓሉ አከባበር ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ለአምስት ደቂቃዎች ብሔራዊ የሕዝብ መዝሙር በመዘመር እና ሰንደቅ አላማም በመስቀል የሚከበር ነዉ። እንዲያም ሆኖ አስተያየት ከጠየቅናቸዉ አንዳንዶች ስለተባለዉ አከባበር ያልሰሙ፤ ሌሎቹም የፖለቲካ ዉጥረት የፈጠረዉ ሳይሆን እንዳልቀረ የገመቱ፤ ስለሀገር ፍቅር መታሰቡ ቢዘገይም አዎንታዊ እንደሆነ ገልጸዉልናል።  የጥቂቱን አስተያየታቸዉን አሰባስበናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ