1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀምቡርግና የባህር ዳር ዩንቨርስቲዎች ስምምነት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 7 2007
https://p.dw.com/p/1GEnU

« ጀርመን በነበርኩበት ጊዜ መዲና በርሊን ላይ በሴሜቲክ ቋንቋዎች በተለይ በግዕዝ ላይ ልዩ ጥናትን አድርጌ ሶስተኛ ዲግሪዬን ጨርሼ ነዉ ወደ ኢትዮጵያ የተመለስኩት። ጀርመን ዉስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ይሰጣል። ለምሳሌ የአፍሪቃና የኤዥያ ጥናት አለ። ሀንቡርግ ከተማ ዉስጥ በሚገኘዉ ዩንቨርስቲ በአፍሪቃ ጥናት ስር የኢትዮጵያ ጥናት ይሰጣል። በዚህ ጥናት ስር ታድያ የትግርኛ ፤ የአማርኛ የግዕዝ አልያም በሌሎች ቋንቋዎች ላይ ለየት ያለ ጥናት እና ምርምር አድርጎ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪን ማግኘት ይቻላል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን ይህ እስካሁን የለም፤ ገና አልተጀመረም። »

በግዕዝ ትምህርት የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በጀርመን ያጠናቀቁት፤ ዶክተር ሙሉቀን አንዷለምየሰጡን አስተያየት ነዉ። ባለፈዉ ሰሞወን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞአል። የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ተቋማት በተለይ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህል ጥናት ላይ በጋራ ለመሥራት ነዉ ያቀዱት። በዕለቱ ዝግጅታችን የሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎቹበጋራ የመስራት ፋይዳ ምን እንደሆነ የሚነግሩንን የሁለቱን ተቋማት ባልደረቦች በእንግድነት ይዘናል።