ዜድቲኢ ኩባንያ እና ከስራ የተሰናበቱት ሰራተኞቹ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 9 2004ዜድቲኢ ( ኤችኬ ) ሊሚትድ ኢትዮጵያ- ኢትዮጵያ ዉስጥ በቴሌኮም ሥራ ላይ የተሰማራ የቻይና ኩባንያ ነው። የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ፤ አቶ እምባይብል አበበ እንደሚሉት ኩባንያዉ የስንበት ደብዳቤ ባገኙ ማግስት 59 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ሠራተኞቹን ከሥራ አሰናብቷል። የመስሪያ ቤቱ የአገር ውስጥ ጉዳዮች የሠራተኛ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሔኖክ ወንድማገኝ ፤ ሠራተኞቹ ከሥራ የተሰናበቱበትን ዋና ምክንያት እንዲገልፁልን ጠይቀናቸዋል።
ሠራተኞቹ በሥራ ገበታ ሳሉም ብዙ ያልተሟላቸው ነገር እንደነበር፤ አንዲት ወይዘሮ ነግረውናል። ምንም አይነት የሠራተኛ መታወቂያም ሆነ የውልና የቅጥር ደብዳቤ አልነበረንም ነው ያሉት። አሁን ደግሞ ባንዴ ከሥራ መሰናበታቸውን ለዶይቸ ቬለ አስረድተዋል። ኩባንያው በበኩሉ፤ ለሠራተኞች የሚገባውን በሙሉ እንዳደረገ እና በገጠመው የሥራ ሂደት ማሻሻል ሠራተኞቹን እንዳሰናበተ ይናገራል። ከሥራ የተሰናበቱ ሠራተኞችም የሰጡን አስተያየት አለ።
እስከ ቅርብ ቀናት የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ኃላፊ የነበሩት ፤ አቶ እምባይብልም ኩባንያው ህግ እንደማያከብር፤ ምንም አይነት የእውቀት ልውውጥ እንደማይደረግ እና ኢትዮጵያዊው ተቀጣሪ ቁጥር በአንፃሩ ትንሽ ነው ይላሉ።
ተቀጣሪዎቹ የጤና መድህን ዋስትና ስለሌላቸው ከኩባንያው ጋ ስምምነት ባለው ሀያት ሆስቲታል ሳይሆን በግላቸው ሌላ ቦታ ታክመው ሂሳቡ እንደሚወራረድላቸው ሲገልፁ አቶ ሔኖክ ይህንን በማጣጣል ሠራተኞቹ በሀያት ሆስቲታልም በግልም መታከም እንደሚችሉ እና ሂሳቡ እንደሚከፈል ነው ያሳወቁን። ኩባንያው ህግ አያከብርም ለሚለው ወቀሳ አቶ ሔኖክ መልሳቸው ምንድን ነው? ይህ ኩባንያስ በኢትዮጵያ ህግ እና ደንብ መሠረት መሥራት አልነበረበትም ወይ?
ለጥያቄዎቻችን በሙሉ ያገኘነቸውን መልሶች ከሙሉ ዘገባው ያድምጡ ።
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ