"ዛፍ ትከሉ ከፍቷል ዘመኑ"-አቶ በያን ተሰማ
ሰኞ፣ ሐምሌ 17 2009ማስታወቂያ
ከአስር አመት በፊት ድሬዳዋን ባጥለቀለቀዉ ጎርፍ ሰባት ቤተሰቦቻቸውን የተቀሙት አቶ በያን ተሰማ ከተፈጥሮ ጋር ግብግብ ገጥመዋል። ሐምሌ 29 ቀን 1998 ዓ.ም. ሌሊት በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ከአቶ በያን ቤተሰቦች በተጨማሪ በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ቤት ንብረትም ወድሟል። አቶ በያን ቤተሰቦቻቸውን በጎርፍ የተነጠቁባትን ቀንም ይሁን የአደጋውን ምክንያት የዘነጉ አይመስልም። ወደ ድሬዳዋ የተጓዘዉ ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር ባጠናቀረው ዘገባ አቶ በያን ጎርፉን መሰሉን አደጋ ለመቋቋም "ዛፍ ትከሉ ከፍቷል ዘመኑ" እያሉ ነው ይለናል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ