ተቃውሞ በዙማ ላይ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 24 2009ማስታወቂያ
የደቡብ አፍሪቃ ፓርላማ የተለያዩ የሙስና ክሶች በቀረቡባቸው የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ ላይ በመጪው ሳምንት የመታመኛ ድምጽ ሊሰጥ ነው ። ድምፅ የሚሰጠው የሀገሪቱ የፀረ ሙስና መስሪያ ቤት ያቀረበው ሪፖርት ይፋ ከሆነ በኋላ ዴሞክራቲክ አልያንስ የተባለው የደቡብ አፍሪቃ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ዛሬ በዙማ ላይ የመታመኛ ድምጽ እንዲሰጥ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ነው ። በርካቶችአደባባይ በመውጣት ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል ። ዙማ ከዚህም ቀደም ሁለት ጊዜ የመተመኛ ድምፅ ማለፍ ችለዋል ።የጆሀንስበርጉ ወኪላችን መላኩ አያሌው ዝርዝር ዘገባ አለው ።
መላኩ አያሌው
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ