ዘረኝነት በብሪታንያ እየከፋ ነዉ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2008ማስታወቂያ
የብሪታንያ ጥቁሮች እና ሌሎች አናሳ ዝርያ ያላቸዉ ዜጎች በቆዳ ቀላማቸዉና በዘራቸዉ ምክንያት የሚደርስባቸዉ በደል ባለፉት ዓምስት አመታት ዉስጥ እየከፋ መምጣቱን በቅርቡ ይፋ የሆነ ጥናታዊ ዘገባ አጋለጠ።በጥናቱ መሠረት የጥቁሮችና የሌሎች አናሳ ዝርያ ያላቸዉ የብሪታንያ ዜጎች ኑሮ ከነጮቹ ጋር ሲወዳደር እጅግ የከፋ ነዉ።ጥቁሮቹ ወይም የአናሳ ዝርያ ተወላጆች ትምሕርት፤ ሥራ፤ፍትሕና የጤና አገልግሎት ለማግኘት ያላቸዉ ዕድል ከነጮቹ ጋር ሲነፃፀር እጅግ ጠባብ ነዉ።ተመሳሳይ የትምሕርት ደረጃ ባላቸዉ ጥቁሮችና ነጮች መካከል ያለዉ የክፍያ ልዩነትም 23 በመቶ ይደርሳል።
ሐና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ