1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘመን አልሽረዉ ያለዉ የድርቅና ርሃብ አደጋ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ሚያዝያ 29 2009

ኢትዮጵያ ዉስጥ በድርቅ የተጠቁና ለምግብ እጥረት የተዳረጉ ወገኖች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ እየተገለጸ ነዉ። መንግሥት ድርቁ የሰዉ ሕይወት ከሚቀጥፍበት ደረጃ እንዳይደርስ ማድረግ መቻሉን ቢናገርም የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ከ7,5 ሚሊየን በላይ  ሕዝብ  መኖሩን አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/2cVMV
Äthiopien Hunger Hungerhilfe
ምስል picture-alliance/dpa/M. Ayene

የለጋሽ ሃገራትን ርዳታም እየጠየቀ ነዉ። የለጋሾቹ ምላሽ ግን እስካሁን የሚያረካ እንዳልሆነ ነዉ የሚገለጸዉ። ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በድርቅ እየተጠቃች ብዙዎችም ለርሃብ አደጋ ሲጋለጡ ታይቷል። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት የእንወያይ መሰናዶዉ፤ «ዘመን አልፎም ዘመን አልሽረዉ ስላለዉ የምግብ እጥረት ጉዳይ፤ ዘላቂነት ያለዉ በምግብ እህል ራስን የመቻል ምኞትና ተግዳሮቱን ለመዳሰስ ይሞክራል። ከድምጽ ዘገባዉ ዉይይቱን ይከታተሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ