1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘመን ተሻጋሪዉ የአፍሪቃ ሃገራት ችግር

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 27 2009

በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር በ2016 ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪቃ ሃገራት የፖለቲካ ችግሮቻቸዉን ሳይፈቱ ወደ 2017 መሸጋገራቸዉ አሁንም አደጋ እንዳለዉ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የወቅታዊ ጉዳይ ተንታኝ አመለከቱ።

https://p.dw.com/p/2VLnq
Äthiopien Anti-Regierungs-Protesten
ምስል REUTERS/T. Negeri

M M T/ Beri. Washington DC (Sub-Saharan Africa 2017) - MP3-Stereo

 በኢትዮጵያ የተነሳዉን የመብት ጥያቄ በማሠር፣ በመግደል፣ በደቡብ ሱዳን ጎሳን መሠረት ያደረገዉ የእርስ በርስ ጦርነት፣ የጋምቢያ ምርጫ ሌሎችም የአካባቢዉ ሃገራት ችግሮች መፍትሄ ሳያገኙ እንደታፈኑ ወደ አዲሱ ዓመት የተሸጋገሩ ታላላቅ ጉዳዮች መሆናቸዉንም ይናገራሉ። እንደተንታኙ የችግሩ መንስኤ ደግሞ በጠብመንጃ የመጡ መንግስታት ያለጠብመንጃ ስለማይወርዱ ነዉ። ዝርዝሩን ከዋሽንግተን ዲሲ መክብብ ሸዋ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ