ዓለም ዓቀፍ ፀረ-ባርነት ቀን
ሰኞ፣ ኅዳር 23 2006መግለጫ የ ተመድ ጠ/ጉባዔ የባርነት ማስወገጃ ድንጋጌን መቀበሉን ያመለክታል። የሰዎች ህገወጥ ዝውውር የሚያስከትላቸውን ቀውሶች እና ሌሎች በተለያዩ መልኮች የሚከሰቱ ብዝበዛዎችን ለመቃወም የድርጅቱን አቐም ም ያንጸባርቃል።
የዚህ ዕለት የትኩረት ኣቅጣጫም በመግለጫው መሰረት ዘመናዊ የባርነት ገጽታዎችን ማለትም ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ወሲባዊ ብዝበዛዎችን የህጻናት የጉልበት ብዝበዛን ከፍላጎት ውጪ የሚፈጸሙ ጋብቻዎችን እና ህጻናትን ለጦርነት የሚዳርጉ ሁኔታዎችን ማስወገድ ነው። በየዓመቱም በተለያዩ መፈክሮች ሲታሰብ ቆይቷል። በዚሁ መሰረት የ ተመድ በ 2007 ዕለቱን አትላንቲክ ውቅያኖስን ኣቐጦ ይካሄድ የነበረው የባርያ ንግድ የተወገደበትን 200ኛ ዓመት በማሰብ ማክበሩ የሚታወስ ሲሆን በ 2008 ም እንዲሁ የኣትላንቲክ ማዶው የባሪያ ንግድ ሰለባዎች ማስታወሻ በሚል መሪ ቃል መከበሩ ኣይዘነጋም።
የ ተመድ ዋ/ጸኃፊ ኮፊ ኣናንም የዛሬው ዕለት እኣኣ ማለት ነው ታህሳስ 2 ቀን 2013 በተለያየ መልኩ ድሆችን የተገለሉ የህ/ክፍሎችን ስደተኞችን በተለይም ሴቶችን በማንነታቸው የተጨቆኑ ወገኖችን እና ኣናሳ የህ/ክፍሎችን የሚያጠቃውን ዘመናዊ የባርነት ገጽታን ለማስወገድ ልዩ ትኩረት መስጠታችንን ያመለክታል ሲሉ መልዕክታቸውን ኣስተላልፏል።
በኣሁኑ ጊዜ በዓለማችን 21 ሞሊየን ያህል ሴቶች ወንዶችና ህጻናት በእጃዙር ባርነት ስር ይገኛሉ ያለው ዓ/ዓቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ILO በበኩሉ ባርነት ኣሁኑኑ ይቁም በሚል መሪ ቃል ታዋቂ አርቲስቶችን ኣትሌቶችን እና የህግ ባለሙያዎችን ኣሰማርቶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ኣስታውቐል። ይሄው የባርነት ገጽታ ከኢትዮጵያ ኣንጻርም በተለይ በስደተኞችና ሴቶች ላይ ይበልጥ እንደሚንጸባረቅ የገለጹት የILO የ ኢትዮጵያው ጽ/ቤት የቴክኒክ ዋና ኣማካሪ ወ/ሮ ኣይዳ አወልም በቅርቡ ከሳውዲ አረቢያ እየተመለሱ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለዓብነት ያህል ጠቅሷል።
በህጋዊ መንገድ የሚሄዱትን ጨምሮ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተለይም ሴቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእጃዙር ባርነት ሰለባ ናቸው የሚሉት ወ/ር ኣይዳ በቅርቡ ወደ ኣገር ቤት የተመለሱትን ተመልሰው እንዳይሄዱ ወይንም እሂዚህም ለከፋ ችግር እንዳይዳረጉ ድርጅታቸው ILO የመልሶ ማቐቐም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንም ጠቅሷል።
ጃፈር ዓሊ