1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ጉባዔ፣

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 20 2001

"ሣይንሣዊ ዕድገትና ፈጠራ፤ ዕውቀትና ምጣኔ ሐብት" በሚል መርሆ በነገው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ የዓለም የመረጃና የግንኙነት ቴክኖሎጂ ጉባዔ ይከፈታል።

https://p.dw.com/p/Hg1y
ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ጉባዔ፣
ከ 3 ዓመት ከመንፈቅ በፊት፣ ቱኒስ አቅራቢያ ክራም ውስጥ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ጉዳይ ጉባዔ፣ የዓለም አቀፉ የመገናኛ ኅብረት ዋና ጸሐፊ ጃፓናዊው፣ ቶሺዋ ዑትሱሚ፣ የያኔው የ ተ መ ድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናንና የቱኒሲያው ፕሬዚዳንት፣ ዚኔ ኧል አብዲኔ ቤን አሊ፣ምስል AP

ሶሥት ቀናት የሚፈጀው ጉባዔ የሚካሄደው በተባበሩት መንግሥታት የስብሰባ ማዕከል ውስጥ ሲሆን ዓላማው አፍሪቃ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከተደቀኑባት የዕድገት ችግሮች መላቀቅ የምትችልበትን መንገድ ማፈላለግ ነው። ጭብጥ የመፍትሄ ሃሣቦችን ለማፍለቅም ይታሰባል። በጉባዔው ላይ ከዓለም ዙሪያ ተተጓዙ ከ 500 የሚበልጡ የዘርፉ ጠበብት እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ዛሬ ከወዲሁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልተዋል። ወኪላችን ታደሰ እንግዳው በቦታው ተገኝቶ ነበር፤ ያጠናቀረው ዘገባም የሚከተለው ነው።

መሥፍን መኮንን፣

ተክሌ የኋላ፣