1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውጊያ በምሥራቃዊ ኮንጎ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 20 2006

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ምሥራቃዊ አካባቢ «ኤም 23» በመባል በሚታወቀው የዓማፅያን ቡድን እና በመንግሥት መካከል ጥቃቱ ዛሬም መቀጠሉ ተገለጸ።

https://p.dw.com/p/1A9Ew
GettyImages 163804113 Congolese M23 rebels fleeing to Rwanda sit on the ground as they are presented to the press on March 16, 2013 in Gasizi, 30km north of Gisenyi, at the border with Democratic Republic of Congo. Fighting between rival factions of Congolese rebel group M23 has sent hundreds of people, including many rebels, fleeing for neighbouring Rwanda, where the leader of one faction has been detained, Rwandan officials said on March 16. AFP PHOTO / STEPHANIE AGLIETTI (Photo credit should read STEPHANIE AGLIETTI/AFP/Getty Images)
ምስል Stephanie Aglietti/AFP/Getty Images

በሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ካለፈው የሣምንት መጨረሻ ወዲህ እንደገና በመካሄድ ላይ ባለው ውጊያ «ኤም 23» በኮንጎ ጦር ትልቅ ሽንፈት እንደደረሰበት በሀገሪቱ የተሰማራው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ ገልጾዋል። በወታደራዊ ርምጃ የሚገኝ ድል ብቻውን ግን ምሥራቃዊ ኮንጎን እንደማያረጋጋ አክሎ አሰረድቶዋል።

በምሥራቃዊ ኮንጎ እንደገና በጦሩ እና ባማፂው ቡድን «ኤም 23» መካከል በቀጠለው ውጊያ የመንግሥቱ ጦር ዛሬ የዓማፅያኑ ጠንካራ ሠፈር ከሆኑት መካከል አንዱ የሚባለውን ቡናንጋን መያዙን አስታውቋል። ቀደም ባሉ ቀናትም የጦር ኃይሉ ከጎረቤት ርዋንዳ ጋ በሚያዋስነው ድንበር የሚገኙ የኪዋንዣ እና የሩትሹሩ መንደሮችን እና የሩማንጋቦ የጦር ሠፈርን ከዓማፅያኑ ማስለቀቅ መቻሉን ገልጾዋል። በአዲሱ የጦር ዘመቻው ላይ በኮንጎ በተሰማራው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ የሚረዳው የኮንጎ ጦር በምሥራቃዊ የሀገሩ ከፊል ያለፉት ሀያ ወራትን የቀጠለውን ዓመፅ ለማብቃት የ «ኤም 23» ጠንካራ ሠፈሮች ወደሆኑት ምቡዚ እና ሩንዮኒንም እየገሰገሰ መሆኑን አንድ ያካባቢው ነዋሪ ለዜና ምንጭ ሮይተርስ በስልክ ገልጾዋል። የ«ዩኤንኤችሲአር» ተወካይ ሉሲ ቤክ እንዳስታወቁት፣ ከ5000 የሚበልጡ ያካባቢው ነዋሪዎች አዲሱን ውጊያ እየሸሹ ወደ ዩጋንዳ ተሰደዋል።
በኬንያ የሚገኙ የፖለቲካ ተንታኝ አህመድ ራጃብ እንደጠቆሙት ግን፣ የመንግሥቱ ጦር በጎረቤት ርዋንዳ ይረዳል የሚለውን «ኤም 23»ን ከብዙ አካባቢ ቢያስለቅቅም፣ በምሥራቃዊ ኮንጎ አዲስ ከተቋቋመ እና ራሱን «ኤም 18» ብሎ የሚጠራ ሌላ ያማፅያን ቡድን አዲስ ጥቃት ያሰጋዋል።
« የ«ኤም 23» ተዋጊዎች በርግጥ የጦሩን ጥቃት ለመቋቋም መታገላቸው ባይቀርም፣ ከያዙዋቸው ሠፈሮች በኮንጎ ጦር ከመባረራቸው በፊት እንደነበሩት ጠንካራ አይሆኑም። ይሁንና፣ አሁን የተቋቋመው ራሱን «ኤም 18» ብሎ የሚጠራው አዲስ ያማፅያን ቡድን የ«ኤም 23» ዓማፅያንን ለማጥፋት እና በምሥራቃዊ ኮንጎ ሰላም ለማውረድ እየሞከረ ላለው የሀገሪቱ መንግሥት ግዙፍ ችግር ይፈጥርበታል። »
በኮንጎ 3000 ወታደሮች ያሰለፈው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ መሪ ማርቲን ኮብለር ጓዱ የሕዝቡን ደህንነት የማስጠበቁን እና አካባቢውን የማረጋጋት ተልዕኮውን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ቢገልጹም፣ ወታደራዊ ርምጃ ብቻውን መፍትሔ እንዳልሆነ በማመልከት ተቀናቃኞቹ ወገኖች ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ እንዲመለሱ ጠይቀዋል ።
« ሲቭሉን ሕዝብ የመከላከል ኃላፊነት አለብን። ይህንኑ ተልዕኳችንን ለመወጣት ነው እዚህ ያለነው። ከዚሁ ጎን ለጎን ግን ውዝግቡን ለማብቂት የሚያስችል ፖለቲካዊውን መንገድ መከተል ይኖርብናል። »
ይህ ግን በወቅቱ የሚሳካ አይመስልም። ያለፉት 12 ወራትን በሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል በካምፓላ ዩጋንዳ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ድርድር ከጥቂት ቀናት በፊት ካላንዳች ውጤት ተበትኖዋል። ለዚህም ዓማፅያኑ ለቡድናቸው መሪ ምሕረት እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተጠያቂ መሆኑ ተገልጾዋል። የትላልቆቹ ሀይቆች አካባቢ የአብያተ ክርስትያን ድርጅቶች ጥምረት የኮንጎ ተመራማሪ ኢሎና አወር ፍሬገ እንደሚሉት፣ የኮንጎ መንግሥት ያማፅያኑን ጥያቄ በመቀበል ፈንታ ጥቃቱን ማጠናከሩን ነው የመረጠው። ይህ ርምጃው ግን ሰላም ማምጣቱን ይጠራጠሩታል፣
« ያማፂውን ቡድን ላጭር ጊዜ ከጎማ ማባረር (ማስወጣት)ቢችልም፣ ለውዝግቡ መፍትሔ አገኘ ማለት አይደለም። እንዳዲስ ተሰባስበው እና የጦር መሳሪያ ትጥቃቸውን አሟልተው ወደ ቀጣዩ ፍጥጫ ያመራሉ። »
የ«ኤም 23» ዓማፅያን አዲሱ ውጊያ ቶሎ ካላበቃ በስተቀር ከሰላሙ ድርድር እንደሚርቁ ነው ቢዝቱም፣ የኮንጎ መንግሥት ዓማፅያኑ ትጥቃቸውን ካልፈቱ ጥቃቱን እንደሚያጠናክር ነው ያስታወቀው።

GettyImages 178265177 The head of the UN Stabilization Mission in the Democratic Republic of Congo (MONUSCO) and special envoy of the UN secretary-general, Martin Kobler (R), gives a press conference on August 28, 2013 at the headquarters of the UN peacekeeping mission in Kinshasa. UN attack helicopters joined Congolese government troops in an operation on August 28 against rebels in the east of the Democratic Republic of Congo, the UN peacekeeping force said. The operation against M23 rebels in the hills of Kibati north of the regional capital Goma also involved UN and DR Congo army artillery. AFP PHOTO / JUNIOR D. KANNAH (Photo credit should read JUNIOR D.KANNAH/AFP/Getty Images)
ምስል Junior D.KannahAFP/Getty Images)
M23 rebellion Major John (L) and Colonel Bildunterschrift: M23 rebellion Major John (L) and Colonel Vianney Kazarama walk as they explain that the M23 does not support Bosco Ntaganda, the chief of staff of another regional militia the National Congress for the Defense of the People, at the Kavumu hill in rebel-held territory in North Kivu, eastern Democratic Republic of the Congo (DRC), on June 3, 2012. An AFP correspondent in Congo and an independent French journalist were briefly detained on June 3 by M23 forces in the Virunga region and then interrogated by civil intelligence officers before being released. Fighting between M23 rebels and Congolese soldiers resumed on June 4 in the Virunga park where the rebel movement embroiled in cat-and-mouse clashes with loyalist troops for weeks has been holding its position on the hills of Runyonyi. AFP PHOTO / MELANIE GOUBY (Photo credit should read Melanie Gouby/AFP/GettyImages) Erstellt am: 05 Jun 2012
ምስል Melanie Gouby/AFP/GettyImages

ሂልከ ፊሸር/አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ