1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት

ነጋሽ መሐመድ
እሑድ፣ ኅዳር 4 2009

እኝሕ ሰዉ ለምን ተመረጡ? ዩናይትድ ስቴትስ የምትመራዉን ዓለምና የፖለቲካ ሥርዓቱን ወዴት ይወስዱታል?

https://p.dw.com/p/2SdhP
Infografik US-Wahl Ergebnis 13. November Deutsch

ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት እንዳሉት የሙቀት ልቀት መጠንን ለመቀነስ አምና የተደረሰበትን ሥምምነት ያፈርሳሉ።ዩናይትድ ስቴትስ ጃፓንን ጨምሮ ከአስራ-አንድ የፓሲፊክ አካባቢ ሐገራት ጋር ያደረገችዉን ዉል (TPP)ን ይሰርዛሉ።ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና ጋር ያደረገችዉን የንግድ  ስምምነት ያፈርሳሉ።ዩናይትድ ስቴትስ ከኩባ ጋር የነበራትን የግማሽ ምዕተ-ዓመት ጠብ ለማርገብ ያደረገችዉ ስምምነት፤ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታመርት የሚያግደዉን ዉሉ ይሰርዛሉ።የኔቶን ሚናም ለመቀነስ ዝተዋል።እኝሕ ሰዉ ለምን ተመረጡ? ዩናይትድ ስቴትስ የምትመራዉን ዓለምና የፖለቲካ ሥርዓቱን ወዴት ይወስዱታል? ዉይይቱን በድምፅ ይከታተሉ።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ