1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የምርጫ ስርዓትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር

እሑድ፣ ጥቅምት 19 2010

16 ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ በቀጣይ ሊኖራት የሚገባው የምርጫ ስርዓት በሚል ርዕስ ላይ ሰሞኑን ውይይት አካሂደዋል።  ገዢው ኢህአዴግ እና ጥምረት የፈጠሩ 12 የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት ድርድር ላይ የምርጫ ስርዓቱ አብላጫ ድምፅ እና የተመጣጣኝ ውክልናን ያቀፈ ቅይጥ ትይዩ ይሁን የሚለው ሀሳብ ቀርቧል።

https://p.dw.com/p/2mdmE
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ካለፈው የካቲት ወዲህ በቀጠለው ድርድር ላይ ከተነሱት የተለያዩ አጀንዳዎች መካከል ተሀድሶ ያስፈልገዋል የተበለው የምርጫው ስርዓት ዋነኛው ነው።  በዚሁ መሰረትም፣  እስካሁን አምስት ዙር ምርጫ የተካሄደበት የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ስርዓት ወደ ቅይጥ ትይዩ ወደሚል ስርዓት እንዲቀየር ገዢው ፓርቲ ሀሳብ አቅርቧል። ከኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ በስተቀር በድርድሩ የተሳተፉት ሌሎቹ 11 ፓርቲዎች በቀረበው ሀሳብ  ቢስማሙበትም፣ የአተገባበር ሂደቱን በተመለከተ ግን፣ ማለትም፣  ፓርቲዎች በምክር ቤት በሚኖራቸው የመቶኛ ውክልና ጥያቄ ላይ አሁንም ልዩነቶች ስላሏቸው ውይይታቸውን እንደሚቀጥሉ ተሰምቷል።  በዚሁ ድርድር ላይ ስለቀረበው ሀሳብ እና ስለኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት ውይይት አካሂደናል።

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ