ወቅታዊ ሁኔታ እና የመገናኛ ብዙሃን አዘጋገብ፤
እሑድ፣ ጥቅምት 26 2010ማስታወቂያ
በዚህ ወቅት አንዳንዶቹ የተፈጠረዉን አጋጣሚ የዘገቡበት መንገድም ማነጋገሩ አልቀረም። በፕረስ ነፃነት ይዞታዋ በዘርፉ ተቆርቋሪዎች ክፉኛ የምትተቸዉ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተጨባች የሚያሳይ የመደበኛዉ መገናኛ ብዙሃኗ አቅሙ መዳከሙን የሚናገሩ አሉ። ይህም የእየዕለት ክስተቶችን ለማወቅ ሕዝቡ ከማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እንዲጠብቅ እንዳደረገዉም ያስረዳሉ። ይህ ደግሞ ላልተጣራ እና የተከሰተዉንም ግጭት ሊያባብስ ለሚችል ፅንፍ የያዘ የመረጃ ስርጭት ሊዳረግ መቻሉንም ያስገነዝባሉ። የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት የሚታየዉን ጥንቃቄ የሚያሻዉ አዘጋገብ መነሻ በማድረግ የመገናኛ ብዙሃን ኃላፊነት እና ድርሻ ላይ ያተኩራል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምፅ መአቀፉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ