ዋይታ ከጎግ አውራጃ ፤ ጋምቤላ፤
ዓርብ፣ የካቲት 29 2005አደሮች ፣ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተገድለዋል የሚል ጥቆማ ከቀረበልን በኋላ ወደ አካባቢው ስልክ በመደወል ፤ አየን ፤ ሰማን ያሉ ሰዎችን፤ እንዲሁም የጋምቤላን መስተዳድር የፀጥታ ኀላፊ አነጋጋረናል ።
ከሰሞኑ ፤ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች መርኅ ግብር ፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከመጽደቁ በፊት ፣ በፍትኅ ሚንስቴር አዘጋጅነት ፤ ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦችን ለማካተት፤ ይረዳል በሚል እሳቤ፣ የውጭ ሃገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፤ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአፍሪቃ ቀንድ ተጠሪ በተገኙበት ፣ ባለፈው ረቡዕ ውይይት መደረጉን የሚያስረዳ ዘገባ አሰምተን እንደነበረ የሚታወስ ነው።
ስለጉባዔው ከሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የቀረበውንም ትናንት አስደምጠናል። ሰብአዊ መብት ዐቢይ አጀንዳ ሆኖ በተመከረበት ወቅት ፤ እንዴት ከሰብአዊ መብት ይዞታ ጋር የተያያዘ ዋይታም ሆነ ብሶት ተሰማ? በጎግ ወረዳ ጋምቤላ ምንድን ነው የሆነው? ያነጋገርናቸው ያካባቢው ሰዎች እንዲህ ብለውናል።-
ስለዚህ ዋይታም ሆነ ስሞታ መንግሥት ምን ይላል? የጋምቤላ መስተዳድር የፀጥታ ኃላፊ አቶ ጎርደን ኮምግ--
ደቡብ ምዕራባዊው የኢትዮጵያ ክፍል፣ ጋምቤላ፤ ባለፉት 9 ዓመታት ገደማ ፣ ከሰብአዊ መብትና የውጭ ባለወረቶች በዚያ ለግብርና ሰፊ ቦታ ስለማግኘታቸው ፣ የሠፈራ መርኀ-ግብርንም በተመለከተ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ መወሳቱ አይታበልም።
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ