ዊኪ ሊክስና የዓለም ዲፕሎማሲ
ሰኞ፣ ኅዳር 27 2003ማስታወቂያ
ቃዛፊን እና ኔታንያሁን ከጠላትነታቸዉ እኩል-እኩል አስደሰታቸዉ።የቤጂንግና የፒዮንግዮንግን የወዳጅነት ሰንሰለት ፈርቅቆ በተቃርኖ አቆማቸዉ።የአሕመዲንጃድን እና የፑቲንን የቋንቋ-የአቅም ርቀትን ጥሶ ባንድ አገላለፅ-አንድ አደረጋቸዉ።የሳራ ፔለንንና የሒላሪ ክሊንተንን ልዩነት ጥሶ-ባንድ አሳደማቸዉ።የአዉሮጳ አሜሪካኖችን አንድነት ሸርሽሮ-ልዩነታቸዉን፣ የአረብ-እስራኤሎችን የጠላትነት መጋረጃ በርቅሶ ተቀራራቢነታቸዉን አፈጋዉ።ዊኪ ሊክስና-ዘገባዉ።ከሁሉም በላይ ዓለም-ኑሮ ሕይወቱን ሥለሚበይኑት መሪዎቹ የነበረዉን አለመለካከት ለወጠዉ።እንዴት-ለምን? የጂዳ፣ የበርሊን፥ የዋሽንግተን ዘጋቢዎቻችን አብረዉኝ አሉ-ላፍታ አብረን እንጠይቅ።
ነቢዩ ሲራክ
ይልማ ሐ/ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ