የህዝብ ቁጥር መብዛት እና ለሰዉ ልጅ መጠቀሚያ መዋል የሚችለዉ ዉሃ መጠን ማነስ በምድራችን የምግብ እጥረትና የአካባቢ ተፈጥሮ መሽመድመድን እያስከተለ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ። ይህን ችግር ለመቀልበስ የሚረዳዉ ለግብርናዉ ዘመናዊ ቴክኒክ መጠቀምና የተፈጥሮ አካባቢን የማይጎዱ ስልቶችን ሥራ ላይ ማዋል እንደሆነ የተመድ ለዘንድሮዉ የዓለም የዉሃ ሳምንት ያወጣዉ ዘገባ ያመለክታል። ሸዋዬ ለገሠw
ነጋሽ መሐመድ