1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣት አሸናፊ በ«ቤቶች» ድራማ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 25 2006

ወጣት ተዋናይ ነው፤ በተለይ «ቤቶች» በተሰኘው አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ «ይበቃል» የተሰኘውን ገፀባሕሪ ወክሎ በመጫወት ዝናን አትርፏል። ወደ ፊት ዓየር ላይ በሚበቃው የዶቸቬለ ተከታታይ ድራማ ላይም ተሳታፊ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/1AkZY
LbE Produktion in Addis Abeba QUALITÄT
ምስል DW/M.S. Siyoum

አነጋገሩ ፈጣንና የብዙዎቹን ዘመናይ የከተማ ወጣቶች ስልት የተከተለ ነው። በረዥሙ አሳድጎ የጠቀለለው የራስ ፀጉሩ መለያው ይመስላል። በአንድ ቤተሰብ የዕለት ተዕለት ግንኙነት ዙሪያ በሚያጠነጥነው «ቤቶች» በተሰኘው አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ውስጥ አብይ ገፀ-ባሕሪያትን ተላብሰው ከሚጫወቱ ዋና ዋና ተዋንያን ዘንድ ይመደባል። በምናቡ ዓለም ይበቃል በእውኑ ደግሞ አሸናፊ ማኅሌት መጠሪያ ስሙ ነው።


ወጣት አሸናፊ ማኅሌት ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ጃን ሜዳ አካባቢ ልዩ ስሙ ኮርያ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው። አሸናፊ ገና የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ነው ትወናን የጀመረው። በልጅነቱ በህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት ውስጥም ሰርቷል። አሁን በሂደት ራሱን ወደ ዘርፈብዙ ተዋናይነት በመቀየር ላይ ይገኛል።

አርቲስት አሸናፊ ማኅሌት «ቤቶች» በተሰኘው የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ይበቃልን ሆኖ ከተጫወተው የተወሰደውን ነበር ያደመጣችሁት። የቴሌቪዥን ተመልካቹ ወክሎ የተጫወተውን ገፀ-ባህሪ እንደሚያደንቅለትና እንደተቀበለውም ገልጿል አሸናፊ።

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወጣት እንደሚገጥመው ሁሉ የአሸናፊ ወላጆችም ልጃቸው ወደ ጥበቡ ዓለም ከመጠጋቱ ይልቅ ምርጫቸው ትምህርቱ ላይ ቢያተኩርላቸው ነበር። አሸናፊ ከቤተሰቡ ወደ ጥበብ ዓለም የተሳበ ብቸኛው ልጅ ነው።

ወጣት ተዋናይ አሸናፊ ማኅሌት ከትወናው ባሻገር ወደፊት የሚመኘው የድርሰትና የአዘጋጅነት ሙያም እውን እንዲሆንለት እንመኝለታለን። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

አሸናፊ ማኅሌት
አሸናፊ ማኅሌትምስል DW/M.S. Siyoum

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ