1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወግ አጥባቂዎቹ አስተማማኝ ድምፅ አግኝተዋል

እሑድ፣ መስከረም 17 2002

ሽታይማየር የሚወክሉት የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ SPD መጀመሪያ ከተገመተዉም ቁልቁል ወርዶ 148 መቀመጫዎች አግኝቷል

https://p.dw.com/p/JqK8
የCDU/CSU ደጋፊዎች ፌስታምስል AP
በጀርመን አቆጣጠር እኩለ ሌሊት ግድም ይፋ በሆነዉ ዉጤት መሠረት፥ ወግ አጥባቂዉ የአንጌላ ሜርክል እሕትማማች ፓርቲ CDU/CSU ካጠቃላዩ የምክር ቤት መቀመጫ 238ቱን በማሸነፍ-የአንደኝነቱን ሥፍራ ይዟል።ሽታይማየር የሚወክሉት የሶሻል ዲሞክራቶቹ ፓርቲ SPD መጀመሪያ ከተገመተዉም ቁልቁል ወርዶ 148 መቀመጫዎች አግኝቷል።የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ FDP 93 መቀመጫዎችን አግኝቷል።የግራዎቹ ፓርቲ 76 አረንጓዴዎቹ ደግሞ 67 መቀመጫዎችን አሸንፈዋል።
ነጋሽ መሐመድ