1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጀብ እና ማዕበል ጥፋት አደረሰ

ቅዳሜ፣ መስከረም 28 2009

ማቲው የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኃያል ወጀብ እና ማዕበል የ900 ግድም ሔይቲ ተወላጆችን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ሲደርስ መዳከሙ ተገለጠ። ማቲው ያገኘውን እየገነዳደሰ እና እየገደለ በካሪቢያን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የፍሎሪዳ የባሕር ጠረፍ ለ4 ተከታታይ ቀናት ብርቱ ጥፋት አድርሷል።

https://p.dw.com/p/2R2dX
USA Hurricane Matthew in Florida
ምስል picture-alliance/dpa/E. Gay

ማቲው የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኃያል ወጀብ እና ማዕበል የ900 ግድም ሔይቲ ተወላጆችን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ሲደርስ መዳከሙ ተገለጠ። ማቲው ያገኘውን እየገነዳደሰ እና እየገደለ በካሪቢያን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የፍሎሪዳ የባሕር ጠረፍ ለአራት ተከታታይ ቀናት ብርቱ ጥፋት አድርሷል።  በተለይ ከአሜሪካ ክፍላተ-ዓለም እጅግ ድሃ በሆነችው ሄይቲ ቢያንስ ለ877  ሰዎች ሕይወት ኅልፈት ሰበብ ኾኗል። ማቲው ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ የባሕር ጠረፍ የደረሰ ሲሆን፤ ሦስት ሰዎችንም ገድሏል። የግዛቲቱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ነዋሪዎች ለጊዜው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል። በወጀብ እና ማዕበል ልኬት ደረጃ አምስት ተሰጥቶት የነበረው ማቲው ፍሎሪዳ ሲደርስ ወደ አንድ ዝቅ ማለቱም ተገልጧል።  ኾኖም እስካሁን ባሕር ላይ የቆየው ኃያል ማዕበል ከባድ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል ተብሎ ስለተፈራ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቶቻቸው እንዲለቁ እየተደረጉ ነው። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ