1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወይዘሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ እንዲፈቱ በቲዩቢንገን የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር

ዓርብ፣ መስከረም 7 2003

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንዲፈቱ ግፊት ለማድርግ በቲዩቢንገን የሩጫ ውድድር ይካሄዳል። ሁለት የጀርመን የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጥሪ አቀረቡ።

https://p.dw.com/p/PF8J
ቲዩቢንገን- ሩጫውን ታስተናግዳለችምስል picture alliance/dpa

የኢትዮጵያው ታቃዋሚ ፓርቲ የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከእስር እንደለቀቁ እዚህ ጀርመን የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያውያን የመብት ተሟጋች ድርጅት ና ሁለት የጀርመን ባለስልጣናት ጠየቁ ። በጀርመን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፣ በጀርመን ምክር ቤት የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እንደራሴ እና የቱቢንገን ከተማ አስተዳደር አባል በየፊናቸው እንዳሉት ወይዘሪት ቡርቱኳን የታሰሩት በፓለቲካ አቋማቸው እንጂ ሌላ ወንጀል ፈፅመው አይደለም ። ወይዘሪት ቡርቱካን እንዲፈቱ ግፊት ለማድረግ የፊታችን ዕሁድ ቱቢንገን ውስጥ የሩጫ ውድድር ይደረጋል ። መሳይ መኮንን

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ