ወታደራዊው ጁንታና ውጥረት በጊኒ17 ታኅሣሥ 2001ዓርብ፣ ታኅሣሥ 17 2001የጊኒ የቀድሞ ባለስልጣናት የተሰጣቸዉ የ24 ሰዓት የጊዜ ገደብ ሳያልቅ ስልጣን ከተቆናጠጠዉ ወታደራዊ ጁንታ ጋ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸዉን ገለጹ።https://p.dw.com/p/GNYYየላንሳና ኮንቴ ስንብትምስል APማስታወቂያጊኒን ለሃያ አራት አመታት በአምባገነንነት ሲገዟት ቆይተው ባለፈው ሰኞ ያረፉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላንሳ ኮንቴ ዜና ረፍትን ተከትሎ ወታደራዊ ጁንታ የአመራሩን ቁንጮ መቆጣጠሩን ገልፆ እንደነበር ይታወቃል። የቀድሞ የመንግስት ባለ ስልጣናት ዛሬ ዋና ከተማዋ ኮናክሬ ተገኝተው የጁንታው መሪ ሻለቃ ሞሳ ዳዲስ ካማራን ፕሬዚዳንት ማለታቸውም ታውቓል።