1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ እና የተፈጥሮ ሀብትዋ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 15 1998

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ውስጥ የዛሬ ሣምንት እሁድ የመድብለ ፓርቲ ምርጫ ይካሄዳል።

https://p.dw.com/p/E0iO
ኮንጎ ኪንሻሳ
ኮንጎ ኪንሻሳምስል Alexander Göbel
ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ውስጥ የዛሬ ሣምንት እሁድ የመድብለ ፓርቲ ምርጫ ይካሄዳል። ይኸው ሀገሪቱ ከቤልጅየም ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ከአርባ ስድስት ዓመታት ወዲህ በቅርቡ የሚደረገው የመጀመሪያው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ ሁነኛ የመሻሻል ለውጥ ያስገኛል በሚል የኮንጎ ዜጎች ትልቅ ተስፋ አሳድረዋል። ይሁንና፡ ይህንን አባባል የሚጠራጠሩትም ጥቂቶች አይደሉም፤ ምክንያቱም የፖለቲካና የኤኮኖሚ ኃይላት ግዙፉን የኮንጎ የተፈጥሮ ሀብት ለመበዝበዝ የሚያደርጉት ሽኩቻ በምርጫውና በውጤቱ ማብቃቱ አጠያያቂ ነውና። ይህንኑ የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት በመቆጣጠሩ ረገድ በወቅቱ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳረፈው ወገን ማን ነው?