1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያ የተገኘው አፅምና ፋይዳው

ዓርብ፣ ጥር 13 2008

የአንዳንዶቹ አፅሞች የራስ ቅል ከድንጋይ የተሠራ ጦር እንደተሰካባቸው የተገኙ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ሰዎቹ ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመለክቱ ናቸው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/1HiKG
Überreste von Opfern eines Massakers in Kenia gefunden
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Mirazon Lahr

[No title]

ኬንያ ውስጥ የተገኘው ከ10 ሺህ አመት በፊት የተገደሉ የአንድ የጎሳ አባላት ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ አፅም በጥንት ጊዜ የሚደርሱ እልቂቶችና ግጭቶች ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ እንደሚችል ሳይንቲስቶች አስታወቁ። ሳንቲስቶች እንዳሉት ቱርካና በተባለው ሐይቅ አቅራቢያ በተካሄደ ቁፋሮ የተገኘው በአንድ ላይ የታሰሩ እና ከባድ ጥቃት የደረሰባቸው የ12 ሰዎች እንዲሁም የሌሎች 15 ሰዎች አፅም ምናልባትም ሰዎቹ አዳኞች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ይጠቁማል። የአንዳንዶቹ አፅሞች የራስ ቅል ከድንጋይ የተሠራ ጦር እንደተሰካባቸው የተገኙ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ሰዎቹ ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመለክቱ ናቸው። ስለተገኘው አጽምና ስለ ጥናቱ ፋይዳ የናይሮቢውን ወኪላችንን ፋሲል ግርማን በስልክ አነጋግረነዋል።

ፋሲል ግርማ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ