ኬንያ፣ የምርጫ ውጤት እና ውዝግቡ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 3 2009ማስታወቂያ
በአስመራጩ ኮሚሽን ድረ ገጽ ላይ እንደተነበበው፣ እስካሁን ከተቆጠረው 92% የመራጭ ድምፅ መካከል ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ 54 ከመቶ በማግኘት እየመሩ ነው። የመራጭ ድምፅ ከሚከማችበት ዋና ኮምፒውተር ድምፅ ተሰርቋል በሚል የኬንይታ ተቀናቃኝ ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ወቀሳ ካሰሙ በኋላ ነው ተቃውሞ የተነሳው። ስለ ኬንያ ምርጫ እና ስለ ውዝግቡ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኙትን የፖለቲካ ተንታኝ ፍቅረማርያም መኮንንን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ፣ የድምፅ ቆጠራው በወቅቱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገን ነበር በመጀመሪያ የጠየቅኋቸው።
ፍቅረማርያም መኮንን
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ